የ2021 የዓለም አቀፍ የፊጎ አዋርድ ተሸላሚ ዶ/ር መቅደስ ዳባ ማናቸው?

Your browser doesn’t support HTML5

ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር መቅደስ ዳባ በቅዱስ ፓውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የማህጸን እና የጽንስ ህክምና ሃኪም እንዲሁም በኢትዮጵያ  የጽንስ እና የማሕጸን ሃኪሞች ማህበር ፕሬዘዳንት ናቸው፡፡ በቅርቡም ዓለም አቀፍ የጽንስ እና የማህጸን ፌደሬሽን በአለም ዙሪያ በዘርፉ በምርመር አስተዋጽኦ አድርገዋል በሚል የጎርጎሮሳዊያኑ 2021 ዓ.ም ከመረጣቸው ባለሞያዎች መሃከል አንዷ በመሆን የፊጎ አዋርድ/ሽልማት ወስደዋል፡፡