ዋሺንግተን ዲሲ —
Your browser doesn’t support HTML5
የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ብዛታቸው በመቶዎች የተቆጠረ የድርጅቱን ታጣቂዎች ይዘው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ድርጅቱን “ከመጉዳት ይልቅ ያጠናክረዋል” ብለዋል የቀድሞ የሕወሓት ታጋይ ዶ/ር አረጋዊ በርኸ ለቪኦኤ በሰጡት የሰሞኑ ሁኔታ ትንተና፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከወጡት መካከል አሁንም ሱዳን ውስጥ ያሉትን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የትሕዴን ምክትል ሊቀመንበር አቶ መኮንን ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡
የሱዳን ባለሥልጣናት ከስድስት መቶ ከሚበልጡ ታጣቂዎች ላይ ትጥቅ መረከባቸውን ሱዳን ትሪቡን የሚባለው የኢንተርኔት ጋዜጣ አመልክቷል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡