ለሀያ ዓመታት በድንበር ጭቅጭቅ የቆዩት ኢትዮጵያና ኤርትራ ዕርቀ ሰላም ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ጅቡቲም ከኤርትራ ጋር ያላትን የድንበር ጭቅጭቅ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥን ዕርዳታ ጠየቀች።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ለሀያ ዓመታት በድንበር ጭቅጭቅ የቆዩት ኢትዮጵያና ኤርትራ ዕርቀ ሰላም ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ጅቡቲም ከኤርትራ ጋር ያላትን የድንበር ጭቅጭቅ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥን ዕርዳታ ጠየቀች።
በተመድ የጅቡቲ አምባሳደር መሃመድ ሳኢድ ዱዋሌህ ትናንት ባሰራጩት ደብዳቤ ዋና ፀኃፊ ጉቴሬዝ ከፀጥታው ምክር ቤት ጋር ሆነው ሁለቱ ሃገሮች በጋራ በሚቀበሉት መንገድ ለድንበር ጭቅጭቁ ሰላማዊ መፍትኄ እንዲገኝ ሂደቱን እንዲያመቻቹልን እንጠይቃለን ማለታቸውን አሶሼየትድ ፕሬስ ዘግቧል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።