ከደቡብ ክልል የአማሮ ልዩ ወረዳ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች አቤቱታ

ሀዋሳ

በደቡብ ክልል የአማሮ ልዩ ወረዳ አርሶ አደሮች በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን መሽገዋል ያሏቸው የኦነግ ሼነ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ አደረሰብን ባሉት ጥቃት ከሦስት ዓመታት በፊት ከቀያቸውና ቤታቸው ከተፈናቀሉ ከ29ሺህ ዜጎች ውስጥ 11ሺህዎቹ ወደ ቀያቸው ባለመመለሳቸው ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ተናገሩ።

የደቡብ ክልል መንግሥት ወደቀያቸው ያልተመለሱ ዜጎችን ለመመለስ በ10 ሚሊዮን ብር ስምንት መቶ ቤቶችን መገንባት መጀመሩን አስታውቋል።

የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰሎሞን በአጭር ጊዜ መልሶ ለማቋቋም ያልተቻለው መንገድ ስለተዘጋ እና ቡድኖች ተደጋጋሚ ጥቃት ስለሚፈጸም ነው ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ከደቡብ ክልል የአማሮ ልዩ ወረዳ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች አቤቱታ