ከጉጂ ዞኖችና ከአማሮ ቀበሌያት የተፈናቀሉ ዜጎች ሁኔታ

25ሺህ ለሚደርሱ ከጉጂ ዞኖችና ከአማሮ ቀበሌያት ለተፈናቀሉ ዜጎች፣ የተለያዩ አካላት የግል ጥረት በማድረግ ዕርዳታ እያደረጉላቸው መሆኑን ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ተጎጂዎች ተናገሩ፡፡

ግለሰቦች በራሳቸው ጥረት ለሚያደርጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን የቸሩ ተጎጂዎች ፤ ከጊዜያዊ ዕርዳታ በተጨማሪ መንግሥት ሰርተን ወደሚኖሩበት ቀያችን ይመልሰን ሲሉ ተማፅነዋል፡፡

የድጋፍ ሰብሳቢ ኮሚቴ አስተባባሪ የገንዘብና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጋቸው ጠቅሰው ተመሳሳይ ተግባር ሀዋሳና አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

የወረዳው አስተዳዳሪ ህዝቡን ከተጋረጠበት ችግር ከመንግሥት በኩል የተደረገው ጥረትና የተሰጠው ትኩረት በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ገልጿል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ከጉጂ ዞኖችና ከአማሮ ቀበሌያት የተፈናቀሉ ዜጎች ሁኔታ