በአሜሪካ እና ኢትዮዽያ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግኑኝነት እንደሚያስደስታተው፥ በኢትዮዽያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ፐትርሽያ ሃስላክ ገለፁ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
Your browser doesn’t support HTML5
በአሜሪካ እና ኢትዮዽያ መካከል ያለውን ስትራተጂካዊ ስምምዕነት በተመለከተ አምባሳደር ሃስላክ ሲናሩ፣ ኢትዮዽያ ከአፍሪካ በተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተግባር, በኮርያ ጦርነት የተሰማራች የመጀመርያ አገር አውስታው፥ ኢትዮዽያ በርከት ባሉ የመንግስታቱ ድርጅት የሰላም ማስከበር ስራ እየተሳተፈች መሆኗንና በአሁኑ ወቅት በሶማልያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ዳርፉር ሰላም አስከባሪ ኋይል መላኳንም አስረድተዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮዽያን ሰራዊት መገልገያ መሳርያዎችን እንደምታቀርብና የሶማልያ ጦርን በማሰልጠን እገዛ እንደምትሰጥም ተናግረዋል።
ተንታኞች ግን አሜሪካ ከኢትዮዽያ ጋር ያላት ግኑኝነት ሁለት መልክ ያለው መሆኑን፣ በአንድ በኩል ኢትዮዽያ በዓለም-አቀፍ ፀረ ሸብሩ ጦርነት እንድተረዳት ስለምትፈልግ፣ በሌላ በኩል በዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብቶች ዙርያ እንዲሁም የፖለቲካ ምህዳሩን ለተቃዋሚዎች እንድታሰፋ ልትጋፋት አትፈልግም ይላሉ።