900 ሚሊዮን ብር ወጪ የወጣበት የድሬዳዋ ውሃ ፕሮጄክት ዛሬ ተመረቀ፡፡
ድሬዳዋ —
የድሬዳዋ ከተማን የውሃ አቅርቦት ከ45 ፐርሰንት ወደ 90 ፐርሰነት ያሳድጋል የተባለለት የውሃ ፕሮጄክት ዛሬ በውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ፣በከተማዋ ምክትል ከንቲባ መሀዲ ጊሬእና በውሃናፍሳሽ ቦርድ ሊቀመንበሩ አቶ ከዲር ጁሃር ተመርቋል፡፡
በከተማዋ የነበረው የውሃ አቅርቦት እጥረትና የፈረቃ አገልግሎት ከመልካ ጀብዱ በስተቀር ሙሉ በሙሉ ይቀረፋል ተብሏል፤ በምረቃው ስነስርዓት ላይ የተገኙት የውሃና መስኖ ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ መስሪያቤታቸው ድሬዳዋን ወደፊትም በሌሎች ዘርፎች እንደሚደግፍ ተናግረዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5