ድሬዳዋ —
በሴቶች ላይ የሚፈፀም ሁከት እንዲወገድ ግፊት ማሳደሪያ ዘመቻ የሚካሄድበት ዓለምአቀፍ ቀን “ሰላማችን ይስፈን፣ በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚካሄድ ጥቃት ይቁም” በሚል መሪ ቃል ድሬዳዋ ላይ በሰላማዊ ሰልፍ ታስቦ ውሏል።
ሰልፉ ሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ጥቃት በተፈፀመባቸው ሴቶችና ህፃናት ተማሪዎች ላይ ያተኮረ እንደነበረ ታውቋል።
ዕለቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሰላሣኛ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ ነው ዛሬ የታሰበው።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።