የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ እና የአዲሶቹ ዜጎች ተሳትፎ

  • ቪኦኤ ዜና

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የሚፎካከሩት የሪፐብሊካን ፓርቲው እጩ ዶናልድ ትረምፕ እና የዲሞክራቲክ ፓርቲው ተፎካካሪያቸው ካመላ ሄሪስ

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ እና የአዲሶቹ ዜጎች ተሳትፎ

እአአ ሕዳር ሲመጣ ዩናይትድ ስቴትስ በምታካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አሜሪካዊያን ለመጀመሪያ ጊዜ ድምጽ በመስጠት ይሳተፋሉ፡፡

ከነዚህም መካከል እአአ ከ2020 ወዲህ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ የሆኑ ወደ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ የውጭ ሀገር ተወላጆች ይገኙባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እነዚህ አያሌ አዲስ መራጮች ታዲያ በሪፐብሊካን ፓርቲ እና በዲሞክራቲክ ፓርቲ ደጋፊዎች እኩል ለእኩል የተከፋፈሉ በሆኑ ግዛቶች ትልቅ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡

ጄፍ ስዊኮርድ ከቨርጂኒያ ግዛት አ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምጽ የሚሰጡ አዲስ የአሜሪካ ዜጋ ያስተዋውቀናል፡፡