የኢትዮ-አሜሪካዊያን የንግድ ምክር ቤት ተቋቋመ

በሜሪላንድ መንግሥት የተመዘገበ ኢትዮ-አሜሪካን የንግድ ምክር ቤት በሲልቨር ስፕሪንጉ ሞንትጎመሪ ኮሌጅ በጠራው የፊታችን ዕሁድ ከቀትር በኋላ በሚያካሂደው ጉባዔ ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር አስታውቋል።

ጥንስሱ ከተጣለ አሥር ወራትን ያስቆጠረው ይህ የንግድ ምክር ቤት የተቋቋመው ዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ ባሉ 15 የተለያዩ ንግዶች ባለቤቶች ቢሆንም በመላ ዩናይትድ ስቴትስ ያሉ ንግዶችን የማስተባበር ሃሣብ እንዳለው መሪዎቹ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ከአስተባባሪዎችና ከመሪዎቹ የጊዜያዊ ቦርዱ ፕሬዚዳንት አቶ አወቀ ስመወርቅ እና የሂሣብ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሰላማዊት ተፈራ ከቪኦኤ ጋር ተወያይተዋል።

ሙሉውን ቃለ-ምልልስ ከተያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮ-አሜሪካዊያን የንግድ ምክር ቤት ተቋቋመ