በኦሮምያ ክልል የታሰሩ ግለሰቦች ቤተሰቦች አቤቱታ

በምዕራብ ኦሮምያ አንዳንድ ከተሞችና ወረዳዎች ግለሰቦች ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ለወራት መታሰራቸውን ቤተሰቦቻቸው አንዳንዶቹ ለቪኦኤ ገለፁ።

እስራት ከተፈፀመባቸው ስፍራዎች መካከል የምዕራብ ወለጋ ሰዮ ኖሌ ወረዳ አስተዳደርና ፀጥታ ፅህፈት ቤት በወረዳቸው ወንጀል ፈፅመው እንጂ ሸማቂዎችን ትደግፋላችሁ ተብለው የታሰሩ እንደሌሉ አስታውቆ፣ ፖሊስ ወንጀላቸውን እያጣራ ነው ብለዋል።

ከተለያዩ ከተሞች ለሚነሱት የእስራት ቅሬታዎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ሥራ ኃላፊዎች ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ከዚህ በፊት የፀጥታና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ፍርድ ቤቶች ዝግ ስለሆኑ በምዕራብ ኦሮምያ የታሰሩ ግለሰቦች ፍርድ ቤት አለመቅረባቸውንና ምርመራው ጊዜ ወሳጅ መሆኑንም ጭምር ገልፀው ነበር። የኢትዮዽያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ቅሬታው እንዳልቀረበለት ገልጿል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮምያ ክልል የታሰሩ ግለሰቦች ቤተሰቦች አቤቱታ