በእሥር ላይ እያለ ህይወቱ ስላለፈ ወጣት የተሰራ ፊልም

Your browser doesn’t support HTML5

በእሥር ላይ እያለ ህይወቱ ስላለፈ ወጣት የተሰራ ፊልም

በእሥር ላይ እያለ ህይወቱ ላለፈው የቀድሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ጋድሳ ሕርጳሳ ሕይወት ዙርያ የሚያጠነጥን ፊልም ተሰርቶ ተመቋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በቴክኖሎጂ ትምሕርት ክፍል የመጨረሻ ዓመት ተማሪ የነበረው ጋድሳ ሕርጳሳ ነሐሴ 26/1996 በወቅቱ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር በነበረው የኢሕአዴ መንግሥት የደሕንነት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋሉ በፊልም የተሰራው የሕይወት ታሪኩ ያሳያል።

ወንድሙ አቶ ታዬ ሕርጳሳ ጋድሳ በመንግስት ሰዎች ከተወሰደ በኋላ በሁለትኛው ቀን በማዕከላዊ እስርቤት እንዳገኙት ያስታውሳሉ።

ለእስሩ ምክኒያትም በወቅቱ የኦሮምያ ክልል አስተዳደር መቀመጫ ከአዲስ አበባ ወደ አዳማ እንዲዛወር የተወሰነውን ውሳኔ በመቃወሙ እንደነበር ገልጾልናል።

ከሁለት ዓመት የእስር ቆይታ በኋላ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ ጉዳት እንደደተሰበትና ወደ በምኒሊክ ሆስፒታል ለሕክምና ተወስዶ ሕይወቱ ማለፉን ወንዱሙ ተናግሯል።