"አሁን ከተፈቱት ይልቅ እስር ላይ ያሉት ቁጥር በጣም ይበልጣሉ። በርካቶች ናቸው። አገር ውስጥ ያለው ሜዲያ መንግስት ሲፈቅድ ሰው ከተፈታ በኋላ ነው የሚያውቃቸው። አብዛኞቹም እስካሁን በእስር ላይ ሳሉ የደረሰባቸውን በደል እና ሰቆቃ አንድም ቀን ሳይገልጹ አሁን ሲፈቱ ነው፤ ለዜና ግብዓት ብቻ የሚያናገሩት።" ጌታቸው ሽፈራው የቀድሞዋ ነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዘጋቢ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በተወነጀሉበት ጉዳይ ጥፋተኛ የሚያደርገውን የይቅርታ ጥያቄ ፈርሞ እንዲወጣ ተጠይቆ “አላምንበትም” በማለቱ አሁንም በእስር እንዲቆይ የተደረገውን የቀድሞውን የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጨምሮ ቁጥራቸው የበዙ የፖለቲካ ሰዎችና ሌሎች ዛሬም አልተለቀቁም።
ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች አነጋግረን ካሰናዳነው በእስር እና እስረኞች ጉዳይ ላይ ያተኮረ ተከታታይ ዘገባ የመጀመሪያውን አጠር ያለ ጥንቅር ነው።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
ገና ያልተፈቱት ሰዎች ጉዳይ