Your browser doesn’t support HTML5
በአላማጣ ከተማ፣ “የትግራይ ክልልን ስርዓተ ትምህርት መሠረት ያደረገ የትምህርት ምዝገባ ተጀምሯል” በሚል ተቃውሞ ለመግለጽ በወጡ ወጣቶችና "የህወሓት ታጣቂዎች" ሲሉ በገለጿቸው አካላት መካከል ተፈጠረ ባሉት ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
በአማራ ክልል የበጀትና አስተዳደራዊ ድጋፍ የተቋቋመው የከተማው ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ መሆናቸውን የገለፁት ኃይሉ አበራ ለጥቃቱ “በተፈናቃይ ስም ወደ አካባቢው ገብተዋል” ያሏቸውንና “የህወሓት ታጣቂዎች” ሲሉ የጠሯቸውን አካለት ተጠያቂ አድርገዋል።
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስር የተደራጀው የአላማጣ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ መሆናቸውን የገለፁት ዝናቡ ደስታ በበኩላቸው “የሰው ሕይወት ያለፈውና የአካል ጉዳት የደረሰው ሰላም የማይፈልጉ ኃይሎችና የተለየ የፖለቲካ አጀንዳ ያላቸው የታጠቁ ሰልፈኞች በፈጠሩት ግርግር ነው” ብለው ውንጀላውን አስተባብለዋል።
የፌዴራል መንግሥቱን ምላሽ በቀጣይ ይዘን እንመለሳለን፡፡