በግጭት ምክኒያት ከደራሼ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች መቸገራቸውን ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

በግጭት ምክኒያት ከደራሼ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች መቸገራቸውን ገለጹ

በደቡብ ክልል ደራሼ ልዩ ወረዳ በግጭት ምክኒያት የተፈናቀሉ በሺሕዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በችግር ላይ እንደሚገኙ ተናገሩ። አብዛኞቹ መኖሪያ ቤታቸው በመቃጠሉ መፈናቀላቸውን የገለፁት ነዋሪዎች መጠለያ ሳያገኙ ብዙ ቀናትን እንዳሳለፉ ገልፀዋል።

ከክልሉ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ምላሽ ለማድረግ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ምላሽ እንዳገኘን ይዘን እንመለሳለን።

ዘገባውን ያጠናቀረው ዮናታን ዘብዲዮስ ነው።