ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ጥምር መንግሥት አቋቋመች

  • ቪኦኤ ዜና
መንግሥቱ የተዋቀረው ለረጅም ጊዜ የዘገየው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተካሂዶ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ቲሼኬዲ ካሸነፉ በኋላ መሆኑ ነው።

የኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቨስተር ኢሉንጋ ኢሉካምባ ዛሬ በሰጡት መግለጫ “ መንግሥቱ ተቋቁሟል። ፕሬዚደንቱ የማቋቋሚያውን አዋጅ ፈርመዋል፡ ባፋጣኝ ሥራ ይጀምራል” ብለዋል።

በሥልጣን ክፍፍል ስምምነቱ መሰረት ሃያ ሦስቱ አባላት ከፕሬዚዳንቱ የለውጥ ጎዳና ፓርቲ የተቀሩት አርባ ሁለቱ ደግሞ ለቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ የኮንጎ የጋራ ግንባር ፓርቲ አባላት ይወስዳሉ።

ባለፈው ታህሳስ ወር የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በበርካታ የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች የአደረጃጀት መጓደል የታየበት እንደነበር ይታወሳል። የመራጭ መዝገቦች መጥፋት፣ የኤሌክትሮኒክ ድምፅ መስጫዎች ብልሽት፣ የምርጫውን ሂደት በማጓተቱ የምርጫ አስፈፃሚ ባለሥልጣናቱ በጨለማው በባትሪ ለማከናወን ተገደዋል።

በምርጫው ሂደት ሁከትም መፈጠሩ ሲታወስ በምስራቅ ኪቩ አራት ስዎች ተገድለዋል።