በአቢዬ ሰብዓዊ ቀውሱ በብርቱ እንዳሳሰበው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩመን ራይትስ ዋች አስታወቀ
በደቡብ ሱዳን የምትገኘው በነዳጅ ዘይት ሀብታሟ የአቢዬ ግዛት ባለፈው ቅዳሜ በሰሜኑ ጦር ከተያዘች ወዲህ በሺዎች የሚገመቱ ነዋሪዎቿ ተፈናቅለዋል። የሞቱና የተጐዱ መኖራቸው ዝርፊያ መካሄዱ፥ ንብረት መውደሙና፥ ጐጆዎች መቃጠላቸው፥ ከሁሉም በላይ ደግሞ የሰብዓዊ እርዳታው መስተጓጐል በብርቱ እንዳሳሰበው፥ ታዋቂው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት Human Rights Watch በዚህ ሳምንት መግለጫው አስታውቋል።
ሁኔታው በአሁኑ ወቅት ምን ይመስላል? የድርጅቱን የአፍሪቃ ክፍል ዋና ዲሬክተር አቶ ዳንኤል በቀለን አነጋግረናል።
ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ