በዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ቅዳሜ ቻርለትስቪል ቨርጂኒያ ከተማ ውስጥ የነጭ የበላይነት አስተሳሰብ አራማጅ የሆኑ ቡድኖች የጠሩት ሠልፍ፣ ተቃውሞ ገጥሞት በተቀሰቀሰ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱና በርካቶች መጎዳታቸው ይታወቃል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ቅዳሜ ቻርለትስቪል ቨርጂኒያ ከተማ ውስጥ የነጭ የበላይነት አስተሳሰብ አራማጅ የሆኑ ቡድኖች የጠሩት ሠልፍ፣ ተቃውሞ ገጥሞት በተቀሰቀሰ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት መጥፋቱና በርካቶች መጎዳታቸው ይታወቃል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለሁለት ቀናት ያህል ከዘገዩ በኋላ ሰኞ ዕለት “ወንጀለኞች” እና “ወንበዴዎች” ሲሉ የጠሯቸውን ፅንፈኞች ለድርጊቱ አውግዘዋል።
ትላንት እንደገና በአንድ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሲናገሩ ደግሞ በሁከቱ ሁለቱም ወገኖች ሊጠየቁ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል። በዚህም ሳቢያ ከፀረ ዘረኝነትና ቀኝ ፅንፈኞች ብቻ ሳይሆን፣ ከራሣቸው የሪፖብሊካን ፓርቲ አመራሮች ሳይቀር ወቀሳ ተነስቶባቸዋል።
“ዲሞክራሲ በተግባር” ፕሮግራም የነዚህን የነጭ የበላይነት አስተሳሰብ አራማጆች አመጣጥና በህብረተሰቡ ላይ የደቀነውን የመከፋፈል አደጋ በባለሞያ ያስገመግማል።
የዲሞክራሲ በተግባር እንግዳ በካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሳንበርናንዲኖ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የሕግ ባለሞያ የሆኑት ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማሪያም ናቸው፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5