የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ ዋሽንግተን ዲሲ መግባታቸውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባወጣው ዘገባ መሰረት የአቶ ለማ የአሜሪካ ጉዞ ዓላማ በሁለቱ ሃገሮች መካከል ባለው የመከላከያ ትብብር ላይ ለመነጋገር ነው።
የአቶ ለማ መገርሳን የዩናይትድ ስቴትስ ቆይታ አስመልክቶ ዘርዘር ያሉ መረጃዎችን ለማግኘት ና እራሳቸውንም አግኝተን ለማነጋገር እየጣርን ነን።
ተጨማሪ ባገኘን ጊዜ ይዘን እንመለሳለን።