በዚህ ሳምንት መግቢያ ላይ የዩናይትድ ስቴትሷን ሊውዚያና ያወደመው አይዳ የተሰኘው የማዕበል ወጀብ፤ ርዝራዥ በኒውዮርክ እና በኒውጀርዚ ከተሞች ላይ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ የተነሳ ከ 46 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው አለፈ፡፡
በኒውዮርክ ከተማ የአደጋው ተጠቂዎች ሕይወታቸው ያለፈው ምድርቤታቸው ውስጥ ጎርፍ በመግባቱ ሲሆን ብዙዎችም በንብረታቸው ላይ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል፡፡ የኒውዮርክ ከተማ ከንቲባ ቢልዳ ቤልሲዮ ሁኔታው አስከፊ እንደሆነ በመግለጽ ሕይወታቸው ባለፉ ሰዎች ዋጋ ከፍለናል ብለዋል፡፡
በኒውጀርዚ እና ፔንሲልቬኒያ ብዙ የመስጠም አደጋዎች እየተመዘገቡ ነው፡፡ ምንም እንኳን በብሔራዊ የዓየር ንበረት አገልግሎት በኩል የወጀቡ ርዝራዥ ሊያደርሰው ስለሚችለው ጉዳት ማስጠንቀቂያ ወጥቶ የነበረ ቢሆንም የወጀቡ ሃይል ግን ብዙዎችን አስደንግጧል፡፡
አይዳ የተሰኘው ማዕበል ሊውዚያና ግዛትን በካታሪና ማዕበል ከተጠቃች ከ16 ዓመታት በኋላ ነው መልሶ የጎዳት፡፡ ይህን ተከትሎ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን መልሶ በማቋቋሙ ትኩረታችንን እናደርጋለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5