ከሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊ ወጣ ብሎ በሚገኝ ታጃውራ በተባለ ፍልሰተኞች በታሰሩበት ቦታ በተፈፀመ የአየር ጥቃት እስካሁን 44 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። 130 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። የተባበሩትን መንግሥታት ድርጅት ድርጊቱን በእጅጉ አውግዞታል። ጥቃቱ በደረሰበት እስር ቤት የሚገኙ ኤርትራውያን ስለ አደጋው ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ ፤ በአየር ድብደባው ሕይወታቸውን ካጡት ውስጥ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን "የሉበትም" ብለዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ይህንን ጥቃት በእጅጉ አውግዘዋል። አያይዘውም በመጀመሪያ ስደተኞችና ፍልሰተኞች ሊታሰሩ አይገባም፣ ጥቃቱ ከተፈፀመ በኋላም ሰላማዊ ዜጎችና ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ መሆን የለበትም ብለዋል። አክለውም በሜዲትራንያን ባህር በኩል አውሮፓ ለመግባት ሞክረው ከአደጋ እንዲተርፉ የተደረጉትን ፍልሰተኞች ወደ ሊቢያ እንዲመለሱ ሊገደዱ አይገባም። "ምክንያቱም ሊቢያ ለደህንነታቸው አስተማማኝ ሀገር አይደልችምና” ፊሊፖ ግራንዲ አሳስበዋል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)
Your browser doesn’t support HTML5