በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል በሚገኘው የፖሊስ ጽህፈት ቤት አጠገብ ዛሬ መኪና ውስጥ የተጠመደ ከባድ ቦምብ ፍንድቶ ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣኖች ገልፀዋል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
በፍንዳታው 145 ሰዎች እንደቆሰሉ ከነሱም 92 ሲቪሎች መሆናቸውን ምክትል የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር ኾሻል ሳዳት ገልፀዋል።
ታሊባን የአፍጋኒስታን ፖሊስ ማሰልጣና ማዕከል ባለው ቦታ ላይ ጥቃት ማድረሱን ወድያውኑ ተናግሯል።