በአፍጋኒስታን አጥፍቶ ጠፊ ባደረሰው ፍንዳታ የሞትና የመቁሰል አደጋ ደረሰ

  • ቪኦኤ ዜና
በአፍጋኒስታን ኾስት ክፍለ ሀገር ደግሞ አንድ አጥፍቶ ጠፊ በወታደራዊ ሰፈር በሚገኝ መስጊድ ውስጥ ባደረሰው ፍንዳታ ቢያንስ 26 ሰዎች ተገድለው 50 መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ገልጿል።

በአፍጋኒስታን ኾስት ክፍለ ሀገር ደግሞ አንድ አጥፍቶ ጠፊ በወታደራዊ ሰፈር በሚገኝ መስጊድ ውስጥ ባደረሰው ፍንዳታ ቢያንስ 26 ሰዎች ተገድለው 50 መቁሰላቸውን የሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ገልጿል።

የአፍጋኒስታን ብሄርዊ ወታደራዊ ኃይል ቃል አቅባይ ካፒቴን አብዱላ ፍንዳታው የደረሰው የአርብ ፀሎት ላይ በመሆኑ ብዙ ሰዎች ነበሩ ብለዋል።

ቶሎ የተባለው የአፍጋኒስታን የዜና ቴሌቪዥን በዘገበው መሰረት የተገደሉት ሁሉም ማንዶዛይ ወረዳ ላይ ያሉት የብሄራዊ ወታደራዊ ኃይል አባላት ናቸው።