40ኛ ዓመቱን በዳላስ ያከብራል
በዩናይትድ ስቴትሷ የቴክሳስ ክፍለ ግዛት ዳላስ ከተማ የኢትዮጵያውያን ህብረተሰብ ማዕከል ለማህበረሰቡ የነጻ ህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ክሊኒክ እያቋቋመ መሆኑን፣ ለዚህም ከግዛቱ የሕክምና አገልግሎት ተቆጣጣሪ ቦርድ እና ለሕብረተሰብ አገልግሎቶች ፈቃድ የሚሰጠውን የግዛቲቱ አስተዳደር ጽ/ቤት ይሁንታ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
የህብረተሰብ ማዕከሉ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አዲስ ጥበቡ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት ማዕከሉ በቅርቡ የጤና መድህን ሽፋን ለሌላቸው ወይም ያላቸው ሽፋን አነስተኛ ለሆኑ የማህበረሰቡ አባላት የነጻ ህክምና አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ፡፡
በመጭው ቅዳሜ እኤአ ነሀሴ 31 በዳላስ 40ኛው ዓመቱን በተለያዩ ዝግጅቶች የሚያከብረው ማዕከል ጤናን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ሲሰጥ መቆየቱንም የማዕከሉ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አዲስ ጥበቡና የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የዳላስ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡