በዩናይትድ ስቴይትሷ ዳላስ ከተማ በፖሊስ አባላት ላይ ትናንት ምሽት በተካሄደው የተኩስ ጥቃት የተጠረጠሩ ሶስት ሰዎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና አንድ ሰው መገደሉን አስታወቁ።
ዋሽንግተን —
በአፍሪካዊያን አሜሪካዊያን ላይ በዚህ ሳምንት የተከሰቱ ግድያዎችን በመቃዎም በተለያዩ የዩናይትድ ስቴይትስ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን በትናንትና ዕለት በዳላስ ከተማ በተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ ጥበቃ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ላይ በተነጣጠረ የተኩስ ጥቃት አምስት ፖሊሶች መገደላቸውና ሰባት መቁሰላቸውን ታውቋል።
ለሰሜን አትላንቲክ የጦር ትብብር ድርጅት (ኔቶ) ስብሰባ ፖላንድ ዋና ከተማ ቫርሻቫ (ዋርሶ) የሚገኙት ፕሬዝደንት ኦባማ የፖሊስ አባላት ላይ የተፈፀመውን ግድያና የማቁሰል የተኩስ ጥቃት አረመኔአዊ፣ አሳፋሪ እና ሆን ተብሎ የተካሄደ ጥቃት ነው ሲሉ ገልፀውታል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5