በሉዊዚያና እና ሚኒሶታ ክፍላተ ሀገር ሁለት ጥቁር አሜሪካውያን ወንዶች በፖሊሶች ጥይት የተገደሉበት እንዲሁም በቴክሳስ ዳላስ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ አምስት ፖሊሶች በጥይት የተገደሉባት ሳምንት ነው- በዩናይትድ ስቴትስ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
አምስቱን ፖሊሶች የገደለው ታጣቂ ማይካ ኤክሳቪየር ጆንሰን፤ ዳላስ ላይ ከዚያም በላይ ጥፋት ለማድርስ ዕቅድ እንደነበረው የዳላስ ፖሊሶች ተናግረዋል።
የዳላስ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ዴቪድ ብራውን፤ “ተጠርጣሪው ሌሎችም ዕቅዶች እንደነበሩት፡ እናምናለን። ጥቁሮችን ለመቅጣት ተነስተዋልና ታላቅ ርምጃ ወስጄ ዋጋቸውን ልስጣቸው በሚል እኛን ዒላማ ያደረገ ሰው ነበር።” ብለዋል።
ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በአሜሪካውያን መካከል መከባበር እንዲሰፍን ተማጽነዋል።"ጉዳዩን እውነተኛ በሆነ፣ በሰከነና በመከባበር ላይ በተመሰረተ መንገድ መያዝ ኅብረተሰባችንን ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ማንቀሳቀስ ይጠቅማል።” በማለት አስገንዝበዋል።
ፕሬዚደንቱ ነገ ማክሰኞ ወደዳላስ ከተማ ይጓዙና ለተገደሉት ፖሊሶች በተዘጋጀ የጸሎትና መታሰቢያ ሥነ ስርዓት ላይ ንግግር ያደርጋሉ።
የአሜሪካ ድምፁ ፈርን ሮቢንሰን ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጅት ታዬ ታቀርበዋልች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5