"ያለንበት መጠለያ ጣቢያ በላያችን ላይ እንዳይዘጋ ሥጋት አለን" ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከደዳብ

Dadaab Refugee

ኬንያ፣ የሶማሊያ ስደተኞች ይኖሩበት የነበረውን የደዳብ ካምፕ ሠፈሮች እየዘጋች መሆኗን ስደተኞች ተናገሩ። ባለፈው ዓመት "ካምብዮስ" የተባለ የደዳብ ሰፈር የተዘጋ ሲሆን፥ በሚቀጥለው ዓመትም “F2” የተባለው ሰፈር ሊዘጋ እንደሆነ ስደተኞቹ ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል።

ኬንያ፣ የሶማሊያ ስደተኞች ይኖሩበት የነበረውን የደዳብ ካምፕ ሠፈሮች እየዘጋች መሆኗን ስደተኞች ተናገሩ። ባለፈው ዓመት “ካምብዮስ” የተባለ የደዳብ ሰፈር የተዘጋ ሲሆን፥ በሚቀጥለው ዓመትም “F2” የተባለው ሰፈር ሊዘጋ እንደሆነ ስደተኞቹ ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል።

የስደተኞች ቁጥር በማሽቆልቆሉ በደዳብ የሚንቀሳቀሱ የዕርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ቁጥርም ሊቀነስ እንደሆነ የደዳብ የማኅበረሠብ ተወካይ ተናግረዋል።

የኬንያ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ስለ ሁኔታዉ ተጠይቆ መልስ ባይሰጥም፣ አንድ የቢሮዉ ባልደረባ

“ስደተኞች ስለ መጠለያው መዘጋት መፍራት የለባቸዉም” ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

"ያለንበት መጠለያ ጣቢያ በላያችን ላይ እንዳይዘጋ ሥጋት አለን" ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከደዳብ