ሕይወት አሣሿ እና ውኃ አሽታቿ መንኩራኩር በማርስ ላይ

ክዩሪዮሲቲ በማርስ ላይ

ክዩሪዮሲቲ በማርስ ላይ

ክዩሪዮሲቲ በማርስ ላይ የሙሉ ጊዜና የሙሉ አቅም ሥራዋን ሰሞኑን ትጀምራለች፡፡

(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)

“መሬታችንን አየኋት” ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ጠፈር የመጠቀው ሰው ዩሪ ጋጋሪን እንደተመለሰ የተናገረው ነበር፡፡

“አንድ የሰው ልጅ እርምጃ፣ ታላቅ እመርታ ለሰው ልጅ ዘር ሁሉ” ጨረቃን የረገጠው የመጀመሪያው ሰው ኔል አርምስትሮንግ ነው ይህንን ያለው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ኤሮኖቲክስና የጠፈር አስተዳደር - በምኅፃር “ናሣ” የሚባለው የቅርባችንን ሰማዮች አሰሣ እያጠናከረ የሰው ልጅ አዕምሮ የወለዳቸውና እጆቹ የተጠበቡባቸው የምርምር መሣሪያዎቹ ዘለግ ወዳሉ ርቀቶችም እየደረሱ ነው፡፡

ሰው ዘወትር የሚያስበው ለመሆኑ በዚህ የትየለሌ ሁለንተና ውስጥ እኛ ብቻ ነን እንዲህ ዓይነት ፍጡራን? በዚህ ከበላያችን በተንሠራፋው ሰማይ ውስጥ ምን አለ? ማን አለ? ሰው ዘወትር የሚያስበው ጉዳይ ነው፡፡

በእንዲህ ዓይነት ፍለጋዎች ውስጥ ከተሠማሩ መንኩራኩሮች መካከል ሰሞኑን ጎረቤታችን ማርስ ላይ ያረፈችው ክዩሪዮሲቲ እነሆ ውኃ እና የሕይወት ፈለግ እያሸተተች ነው፡፡ ይህ የጠፈር ምርምር ከምርምር ያለፈ ፋይዳ ይኖረው ይሆን? እንደአፍሪካ ዓይነት አሕጉር፣ እንደኢትዮጵያ ዓይነት ሃገር በዚህ መስክ ምን ማየት ይችላሉ?

በማርስ ተልዕኮዎች፣ በክዩሪዮሲቲ ሥራና በሌሎችም ዓለማት አሰሣዎች ውስጥ ጉልህ ተሣትፎ ያላቸውን አንድ የናሣ የሥራ ኃላፊ የሆኑትን ኢትዮጵያዊ ሣይንቲስት ዶ/ር ብሩክ ላቀውን ያዳምጡ፡፡

(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡)