በአገራዊ ምክክሩ፣ የሕዝብ አጀንዳዎች ሙሉ ትኩረት እንዲያገኙ ግፊት እንደሚያደርግ የገለጸው የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት፣ ሂደቱን የሚከታተልበትንና የሚገመግምበትን መርሐ ግብር ዛሬ ሃሙስ ይፋ አድርጓል፡፡
በአሁኑ ወቅት የአገራዊ ምክክር አጀንዳዎችን የማሰባሰብ ሂደቱ “በፍጥነት እየተከናወነ ነው” ያሉት የኅብረቱ ዋና ዲሬክተር መስዑድ ገበየሁ፣ የጥራት ጉድለት እንዳያስከትል ግን ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
ኅብረቱ፣ በክልሎች ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ጋራ ምክክር ማድረጉን አስታውቋል፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ ከአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡