"ኢህአዴግ እንደ ድርጅት አራቱ ድርጅቶች የራሳቸውን ድርሻ በመንግስት የሥራ ኃላፊነት ላይ አስቀምጠው ተግባብተው ወጥተዋል።.. ለኢህአዴግ ተገዥ እንሁን ነው በአጭሩ።" አቶ አሉላ ሰለሞን በሰሜን አሜሪካ የትግራይ ተወላጆች ማሕበር ዳይሬክተር። ይሄ መግለጫ ወዲያ ወዲህ መያዝ አያስፈልገውም። በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ የተደረገ ተግሳጽ፤ ከፍ ካለ ደግሞ እንደ ዛቻ ነው መታየት ያለበት።” አቶ ጀዋርን ማሃመድ የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር።
Your browser doesn’t support HTML5
Your browser doesn’t support HTML5
የኢትዮጵያና ኤርትራን የድንበር ውዝግብ፣ እንዲሁም የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል ይዞታ ለማዛወር የተያዘውን ሃሳብ ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግስት የደረሰበትን ውሳኔ ተከትሎ የሕወሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፈው ረቡዕ ያወጣው መግለጫ አሁንም በስፋት እያነጋገረ ነው።
የሁለት ወገን ዕይታ በመግለጫው ይዘት እና አንድምታ፣ እንዲሁም ሌሎች የወቅቱን የፖለቲካ ይዞታ የሚያስቃኙ ጭብጦች ዙሪያ ትኩረት ያደርጋል። እሰጥ-አገባ።