Your browser doesn’t support HTML5
የሳምንቱን ዜናዎች ተንተርሶ በአገሪቱ የፖለቲካ ትኩሳት ዙሪያ ትኩረት በማድረግ የሚሰናዳው እሰጥ አገባ፤ በአዲስ አበባ እና በዩናይትድ ስቴትሷ ኦስተን በሁለት ጋዜጠኞች መካከል የተጀመረ ክርክር በዛሬው ዕለት ዕውን ወደሆነ አንድ አዲስ ክስተት ይወስደናል።
የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲያነጋግር የሰነበተውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአነስተኛ ድምጽ ብልጫ በዛሬው ዕለት አጽድቋል።
ለመሆኑ ይህ ውሳኔው አገሪቱ ባለችበትም ሆነ በምትሄድበት አቅጣጫ ላይ ምን ዓይነት አንድምታ ይኖረው ይሆን? የዋዜማ የኢንተርኔት ራዲዮ አዘጋጁ አርጋው አሽኔ እና የHorn Affairs የኢንተርኔት አምድ አዘጋጁ ዳንኤል ብርሃኔ ይከራከሩባታል።