በህንድና ፓኪስታን ድንበር ባለው ውዝግብ ሃያ ስድስት ሰዎች ሞቱ

  • ቪኦኤ ዜና
በህንድና ፓኪስታን ድንበር ባለው በአወዛጋቢው የካሽሚር ክልል ሌሊቱን በህንድ ፖሊሶች በተካሄደው የድንበር ተኩስ ልውውጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን የፓኪስታን ጦር አስታወቀ።

በህንድና ፓኪስታን ድንበር ባለው በአወዛጋቢው የካሽሚር ክልል ሌሊቱን በህንድ ፖሊሶች በተካሄደው የድንበር ተኩስ ልውውጥ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከፍ ማለቱን የፓኪስታን ጦር አስታወቀ።

የጦሩ ቃል አቀባይ ሜሸር ጀነራል አስኢፍ ጋሃፎር ዛሬ ዐርብ እንዳስታወቁት፣ ህፃናትንና ሴቶችን ጨምሮ በጠቅላላው 26 ሰዎች ሞተዋል።

ቻርዋ እና ሃርፓል በተባሉት የፓኪስታን መንደሮች ውስጥ የተካሄደውና አያሌ ሰዎቸ የቆሰሉበት ይህ ተኩስ፣ ለመነሻው ምንም ዓይነት ትንኮሳ እንዳልነበረው ቃል-አቀባዩ ጨምረው ገልፀዋል።

በአወዛጋቢው የሂማልያ ክልል የተካሄደው የአሁኑ ክስተት የተቀሰቀሰው፣ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሻሂድ ካቃን አባሲ በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ፣ ህንድ ካሽሚር ውስጥ በርካታ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸሟን በመናገራቸው እንደሆነም ተገልጿል።

“ፓኪስታን ለዚህ ህንድ ካሽሚር ውስጥ ለፈጸመችው አድራጎት፣ ዓለማቀፍ ምርመራ እንዲካሄድ ትጠይቃለች” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።