የዓመቱ ፕሬስ ነፃነት ተሸላሚዎች ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ተዋወቁ።

ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ቡድን CPJ «ጭቆና ባለበት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ለመዘገብ የቻሉ ድንቅ ጋዜጠኞች፤» ሲል፥ ያወደሳቸውንና ለዘንድሮው የፕሬስ ነፃነት ሽልማቱ ያበቃቸውን ጋዜጠኞች ሥራና ማንነት ያስተዋቀበት ሥነ ሥርዓት አካሄደ።

ዋና መቀመጫውን በኒው ዮርክ ያደረገው ለጋዜጠኞት መብት የቆመው ተቋም፥ በዛሬው ዕለት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ባካሄደው በዚህ ሥነ ሥርዓት፥ ከተዋወቁት አራት ተሸላሚዎች፥ በሥነ ሥርዓቱ በአካል መገኘት ሳይችል የቀረውና፥ በአገሩ «በዜጎች ላይ እየደረሱ ናቸው፤» ያላቸውን በደሎች የተመለከቱ ዘገባዎች በኢንተርኔት ድረ ገፁ በማውጣቱ ለእስር የተዳረገው ኢራናዊው ጋዜጠኛ ይገኝበታል።

ከዳዊት ጋር የተካሄደውን ቃለ ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል ያዳምጡ።

http://www.voanews.com/MediaAssets2/amharic/2010_11/CONFIG.SYS