የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ለዓለም ሃገሮች የሚሰጠውን የኮቪድ ክትባት መጠን ከፍ እንዲያደርጉ ተጠየቁ።
ተጨማሪ ዘረመላቸውን የቀየሩ የኮሮና ቫይረስ ዐይነቶች እንዳይከሰቱ ለመከላከል ፕሬዚደንቱ ዩናይትድ ስቴትስ ለዐለም ሃገሮች የምትሰጠውን ክትባት አቅርቦት እንድትጨምር ከ175 በላይ የጤና ጥበቃ አዋቂዎች ሳይንቲስቶችን እና ተሙዋጋቾች ጠይቀዋል።
የጤና ባለሙያዎቹ ይህንኑ አስመልክተው ለፕሬዚደንቱ ደዳቤ መጻፋቸውን ዋስንግተን ፖስት ዘግቧል።
ፕሬዚደንት ባይደን በይበልጥ ተላላፊ የሆኑ የቫይረሱ ዝርያዎች እንዳይነሱ በዐለም አቀፍ ደረጃ ግዙፍ የክትባት ማምረት መርሃ ግብር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አዘጋጅተው እንዲያወጡ ደብዳቤውን የፈረሙት የጤና ጥበቃ አዋቆች ጠይቀዋል። ፕሬዚደንቱ ወረርሲኙን ለመግታት ፥ እስካሁንየተገኙ ውጤቶች እንዳይቀለበሱ
ለወደፊቱም ክትባቶችን የሚመረቱበትን መንገድ ለማደራጀት የበለጠ እንዲሰሩ ተማጽኖ አቅርበውላቸዋል።
የተማጽኖው ፈራሚዎች ሌላም ደብዳቤ ለፕሬዚደንቱ መላካቸውን ፖስት ዘግቡዋል። አፍሪካ፥ ላቲን አሜሪካ እና እስያ ውስጥ በሚሊዮኖች የተቆጠሩ ሰዎች የመጀመሪያ ክትባት እንኩዋን ባላገኙበት ዩናይትድ ስቴትስ 55 ሚሊዮን ክትባቶች አከማችታለች ሲሉ ወቅሰዋል። የባይደን አስተዳደር ዐለም አቀፉን ወረርሲኝ ለመጋፈጥ እየወሰደ ያለው ርምጃ ዝግተኛ ነው ተብሎ ይወቀሳል
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ለዓለም ሃገሮች የሚሰጠውን የኮቪድ ክትባት መጠን ከፍ እንዲያደርጉ ተጠየቁ።
ተጨማሪ ዘረመላቸውን የቀየሩ የኮሮናቫይረስ ዓይነቶች እንዳይከሰቱ ለመከላከል ፕሬዚዳንቱ ዩናይትድ ስቴትስ ለዓለም ሃገሮች የምትሰጠውን ክትባት አቅርቦት እንድትጨምር ከ175 በላይ የጤና ጥበቃ አዋቂዎች ሳይንቲስቶችን እና ተሟጋቾች ጠይቀዋል።
የጤና ባለሙያዎቹ ይህንኑ አስመልክተው ለፕሬዚዳንቱ ደዳቤ መጻፋቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።
ፕሬዚዳንት ባይደን በይበልጥ ተላላፊ የሆኑ የቫይረሱ ዝርያዎች እንዳይነሱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግዙፍ የክትባት ማምረት መርሃ ግብር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አዘጋጅተው እንዲያወጡ ደብዳቤውን የፈረሙት የጤና ጥበቃ አዋቂወች ጠይቀዋል። ፕሬዚዳንቱ ወረርሽኙን ለመግታት እስካሁን የተገኙ ውጤቶች እንዳይቀለበሱ ለወደፊቱም ክትባቶችን የሚመረቱበትን መንገድ ለማደራጀት የበለጠ እንዲሰሩ ተማጽኖ አቅርበውላቸዋል።
የተማጽኖው ፈራሚዎች ሌላም ደብዳቤ ለፕሬዚዳንቱ መላካቸውን ፖስት ዘግቧል። አፍሪካ፣ ላቲን አሜሪካ እና እስያ ውስጥ በሚሊዮኖች የተቆጠሩ ሰዎች የመጀመሪያ ክትባት እንኳን ባላገኙበት ዩናይትድ ስቴትስ 55 ሚሊዮን ክትባቶች አከማችታለች ሲሉ ወቅሰዋል። የባይደን አስተዳደር ዓለም አቀፉን ወረርሽኝ ለመጋፈጥ እየወሰደ ያለው እርምጃ ዝግተኛ ነው ተብሎ ይወቀሳል።