በኦሚክሮን ቫይረሰ የመጣው ወጀብ ማብቂያው ሳይጀምር አልቀረም ተባለ

  • ቪኦኤ ዜና

ሲያትል ውስጥ የጤና ባለሞያዎች የፒሲአር ምርመራ ለማድረግ እየተዘጋጁ እአአ ጃንዋሪ 4/2022

በዩናይትድ ስቴትስ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ቁልቁል ወርዶ በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስ ወደሚችልበት ከፍታ እየወጣ መሆኑን አንድ አዲስ ጥናት ማመልከቱ ተገለጸ፡፡

በዋሽንግተን ሲያትል ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች አሁን በዩናይትድ ስቴትስ ያለው የኮቪድ-19 ሥርጭት ተጋላጮች እለታዊ ቁጥር እኤአ በጥር 11/2014 ላይ ወደ 1.ሚሊዮን እንደሚያደግ የገለጹ ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን በአንድ ጊዜ ወደታች እየወረደ እንደሚመጣ ገልጸዋል፡፡

ተመራማሪዎችይህ የሚሆንበት ምክንያት ለአሶሼይትድ ፕሬስ ሲናገሩ “ምንክንያቱም በተባለው ቀው “ሁሉም ሰው ለቫይረሱ የተጋለጠ ስለሚሆን ነው” ብለዋል፡፡

የእንግሊዝ መንግሥትም በየቀኑ 200ሺ የነበረው የአዲስ ተጋላጮች ቁጥር አሁን ባለፈው ሳምንት ወደ 140ሺ መውረዱን ገልጸዋል፡፡

በሌላም ጥናት የካይዘር ፐርመናንቴ በደቡብ ካሊፎኒያ ባደረገው ጥናት የኦሚክሮን ቫይረስ የሚያደርሰው ከባድ ጉዳት እጅግ አነስተኛ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ወደ ህክምና ተቋማት ከተወሰዱት 70 ሺ የኮሮናቫይረስ ተጋላጮች መካከል 50 ሺ የሚደርሱት የመተንፈሻ መሳሪያ ያልስፈለጋቸውና ያልተገጠመላቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በዚሁ ምርምር ዘገባ ከዴልታ ቫይረስ አንጻር የኦሚክሮን ቫይረስ ተጋላጮች የሆስፒታል ቆይታ እጅግ ያጠረ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በሌሎች ጥናቶችም የኦሚክሮን ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ በታየባቸው እንግሊዝና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተመሳሳይ ሁኔታ መኖሩ ተገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ልዩ ክትባቶች አማካሪ ቦርድ አሁን ያሉት ክትባቶች ኦሚክሮንን ጨምሮ አዳዲሶቹ ቫይረሶችን በመከላከል ረገድ ውጤታ መሆናቸው እንደገና መትፈተሽና መሻሻል ያላባቸው መሆኑን በመግልጽ አስጠንቅቀዋል፡፡