የኮቪድ-19 ማዕበል በኢትዮጵያ

ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ሦስተኛው የኮቪድ-19 ማዕበል መነሳቱን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። በተለይ ከሁለት ሳምንታት ወዲህ የቫይረሱ የስርጭት መጠን በፍጥነት እያሻቀበ መሆኑንም ጠቁሟል።

በዚህ በሦስተኛው ማዕበል እየታየ ያለው በዓለም በቅርብ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣው ዴልታ የተሰኘው የኮቪድ-19 ቫይረስ ዝርያ ስለመሆን አለመሆኑ ግን ገና ጥናት እየተካሄደ ነው ሲሉ ነው የጤና ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ለአሜሪካ ድምፅ የገለጹት።

ባዶ ሆነው የነበሩ የጤና ተቋማት ዳግም በቫይረሱ ተጠቂዎች እየሞሉ ነው ያሉት ዶ/ር ተገኔ ኤካ ኮቶቤ ሆስፒታልን በምሳሌነት ጠቅሰዋል።

የጤና ሚኒስቴር ኅብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ሲልም ጥሪ አቀርቧል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኮቪድ-19 ማዕበል በኢትዮጵያ