ዋሺንግተን ዲሲ —
በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር በፍጥነት ወደ አንድ ሚሊዮን እያሻቀበ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ ማዕከል ዛሬ ማልዶ ያወጣው አሃዝ ያሳያል።
በሽታውን በሚያስከትለው በኮሮናቫይረስ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከሰላሳ ሶስት ሚሊዮን አልፏል።
ሲኤንኤን ቴሌቭዥን የሆፕኪንሱን መረጃ አጥንቶ በዘገበው መሰረት በዩናይትድ ስቴትስ ሃያ አንድ ክፍለ ግዛቶች ለቫይረሱ የተጋለጠው ሰው ብዛት ከቀደመው ሳምንት ከነበረው በአስር ከመቶ ጨምሯል።
በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የጤና ነክ አሃዞች ማጠናቀሪያና መገምገሚያ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ክሪስ መሬ ለሲኤኤን በሰጡት ቃለ መጠይቅ በመጪው ጥቅምት በጣም ይጨምራል ተብሎ የሚጠበቀው የኮሮናቫይረስ ስርጭት በህዳርና ታህሳስም እንደዚያው እንደሚቀጥል ይሰጋል ብለዋል።
በዩናያትድ ስቴትስም የኮሮናቫይረስ ተያዦች ቁጥር ከሰባት ሚሊዮን አልፉዋል። ህንድ ከስድስት ሚሊዮን በላይ ብራዚል ወደአምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ተጋላጮችን ይዘው ይከተላሉ።