ኮቪድ-19 በዓለም

  • ቪኦኤ ዜና

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዥ ኮቪድ-19 በዓለም ዙሪያ ለመገመት የሚያዳግት የከበደ መከራ ሊያስከትል ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

መንግሥታት የመከላከል እርምጃ ካልወሰዱ ከባድ የርሃብ ቸነፈር፣ የገዘፈ ሥራ አጥነት ሊከሰት ይችላል ሲሉ ጉቴሬዥ አስጠንቀዋል።

የበለጸጉ ሀገሮች የየራሳቸውን ችግር መቋቋሚያ ወጭ መድበዋል፤ በመልማት ላይ ላሉት ሀገሮች ግን በአጣዳፊ የሚያስፈልጋቸውን መጠነ ሰፊ እርዳታ ለማድረግ በቂ ትብብር እስካሁን አላየንም ሲሉ ዋና ጸኃፊው ከሀምሳ የዓለም መሪዎች ጋር በኢንተርኔት ባደረጉት ጉባኤ አሳስበዋል።