የኮቪድ-19 ክትባት

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል

ፎቶ ፋይል

የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ፍለጋ ጥረት፣ መልካም አዲስ ዜና ተሰምቷል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ሞደረና ኩባኒያ ሦስተኛና የመጨረሻ ምዕራፍ የሰው ላይ ሙከራ፣ክትባቱን አስመልክቶ በታየው ቅድመ ውጤት ክትባቱ ዘጠና አራት ነጥብ አምስት ከመቶ ውጤታማ ሆኖ መገኘቱን ገልጧል።

ግዙፉ ማሳቹሴትስ የሚገኘው የመድሃኒት ኩባኒያ ሞደርና ከዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የአለርጂ እና የተላላፊ በሽታዎች ኢንስቲቱት ጋር ሆኖ የሰራው ክትባት ነው።

ባለፈው ሳምንትም እንዲሁ የዩናይትድ ስቴትሱ የመዳህኒት ኩባኒያ ፋይዘር ከጀርመን ባዮ ኢንቴክ ጋር ሆኖ የሰራው ክትባት ትልቅ ውጤት ማስገኘቱን ማስታወቁ ይታወሳል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰንም በሰራው ክትባት ላይ የመጨረሻ ደረጃውን የሰው ላይ ሙከራ እንግሊዝ ውስጥ እንደሚጀምር አስታውቋል።

በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 የታያዙት ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ አራት ነጥብ አምስት ከመቶ ማለፉን፣ በበሽታው ህይወታቸው ያለፈው ደግሞ ከአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን ማለፉን የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የወረርሺኙ መረጃ ማዕከል አመልክቷል።