ኮቪድ-19 በዩናይትድ ስቴትስ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ ዴንቨር የአውሮፕላን ጣቢያ

በዩናይትድ ስቴትስ በኮሮናቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን አለፈ።

የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ-19 መረጃ ማዕከል ዛሬ ባወጣው አሃዝ መሰረት የቫይረሱ ተጋላጮች ቁጥር ሁለት ሚሊዮን አራት መቶ ስድሳ አራት ደርሱዋል ፤ በበሽታው ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉት ደግሞ አንድ መቶ አስራ ሁለት ሲህ ዘጠን መቶ ሃያ አራት ደርሷል።

ዩናይትድ ስቴትስ በኮቪድ-19 በተጠቁትም ሆነ ለህልፈት በተዳረጉት ሰዎች ብዛት አሁንም ከዓለም ቀዳሚነቱን እንደያዘች ናት።

ሃያ አንድ የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች በዚህ ሳምንት ከእስካሁኑ ከፍተኛ የቫይረሱ ተያዦች ቁጥር መዝግቧል፤ የሚበዙት አሪዞና፤ ኒው ሜክሲኮ፤ ቴክሳስና ዩታህ መሆናቸው ተገልጿል።

የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች አሃዝ የጨመረው ክፍለ ግዛቶቹ የእንቅስቃሴ ክልከላዎችን እያነሱ ባሉበትና የበጋ ዕረፍት መግቢያ የሚያበስረው ዓመታዊ የሚሞሪያል ዴይ በዓል በተከበረበት በዚህ ሰሞን መሆኑ ተጠቅሷል።