ኮቪድ-19

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል

ፎቶ ፋይል

በዓለም ደረጃ በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 13ሚሊዮን ደርሷል። ከ570,000 በላይ የሚሆኑት ደግሞ በሞት ተለይተዋል።

የቫይረሱን መዛመት ለመገደብ ሲሉ ጥብቅ ኳራንቲን እንዲኖር፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግና የአካል ርቀትን የመከተል መምርያዎች እንዲያከበሩ፣ መንግሥታትበጥብቅ በሚያሳስቡበት ወቅት ነው የቫይረሱ መዛመት እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰው።

ዩናይትድ ስቴትስ በጥቂት ወራት ውስጥ፣ ለክትባትነት የማገልግል መስረት ያላቸው መድሀኒቶችን አመርታለሁ ብላ እንደምትጠብቅ ገልጻለች። /CNBC/ የተባለ የአሜሪካ የቴሌቪዥን ጣብያ ትናንት በዘገበውመሰረት፣ የክትባት መድሃኒት የማምርቱ ሂደት የተጀመረ መሆኑን፣ አንድ ከፍተኛ የትረምፕ አስተዳደር ባለሥልጣን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።