የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ

ዶ/ር ሊያ ታደሰ

በሕብረተሰቡ ውስጥ እየተስተዋለ ላይ ነው ያለው ከፍተኛ ቸልተኝነትና መዘናጋት አሳሳቢ ሁኔታ መፍጠሩን የኮቪድ - 19 ወረርሽኝን የጥድፊያ መዛመት የደቀነውን ስጋት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ያወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ለቫይረሱ የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥር በብዛት እንዲጨምር ምክንያት መሆኑን ጠቅሰው እየታየ ያለው ከፍተኛ ቸልተኝነትና መዘናጋት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የሚያስችል ልዩ ትኩረት እንደሚያሻው የጤና ሚንስቴር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳስበዋል።

በየእለቱም በአማካይ ቁጥራቸው 305 የሚደርሱ በጽኑ የታመሙ ህሙማን በሕክምና ተቋማት የሚገቡ መሆናቸውን ያስረዱት ሚንስትሯ በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙት ከጤና ተቋማት ህሙማንን የመቀበል አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱንም ገልፀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ