በማላዊ ክትባት መወሰድ የሚፈልጉ ታዳጊ ወጣቶች ቁጥር አነስተኛ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባትን ለመውሰድ እየተጠባበቁ ብላንታይር፣ ማላዊ እአአ ማርች 2021

የማላዊ መንግሥት የኮቪድ-19 ክትባትን መውሰድ የሚፈልጉ ታዳጊ ወጣቶች ቁጥር በጣም ዝቅተኛ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ይህ የሆነው ቤተሰቦችና አሳዳጊዎች ልጆቻቸው ክትባቱን እንዲወስዱ የሚያመነቱ በመሆኑ እንደሆነም የመንግሥት ባለሥልጣናት ገልጸዋል፡፡

ማላዊ እኤአ ከጥር 1/ 2022 ጀምሮ እድሜያቸው ከ12 እስከ 17 ለሚሆኑ ታዳጊ ወጣቶች የፋይዘር ክትባትን ለመስጠት ፈቃደኛ ቢሆንም እስካለፈው ቅዳሜ ድረስ ክትባቱን የወሰዱት 4ሺ ብቻ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

የማላዊ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባለሥልጣን ማይለሲ ማሃንጎ በተለይ በመንግሥት እና በግል ትምህር ቤት ያሉ ተማሪዎች ስለክትባቱ ያላቸውን አመለካከት እንደሚከተሉ አስረድተዋል።