የችሎት ዜና

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራር አባል አቶ ደጀኔ ጣፋ እና ሚሻ አደም ላይ ዐቃቤ ሕግ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መሰረተ። ክሱ በሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በመተላለፍ በሕዝብ ደኅንነት ኑሮ ላይ ከፍተኛ ቀውስ ማድረስ የሚል ነው።

በሌላ የችሎት ውሎ ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ጋዜጠኛ ጉዩ ዋረዮስ በዋስ ከእስር መለቀቁን ጠበቃው አስታውቋል።

ጋዜጠኛው ትናንትና በአስር ሺህ ብር የዋስትና መብቱ ተከብሮለት መውጣቱን ነው የህግ ጠበቃዉ አቶ ደጀኔ ፍቃዱ ለአሜሪካ ድምፅ ያስረዱት።

በሌላም በኩል የኢዴፓ አመራር አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው ከእስር ባለመለቀቃቸው የዋስትና መብት መጠየቂያ አቤቱታ ለቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ማስገባታችውን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የችሎት ዜና