የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ሦስተኛ ምድብ ችሎት የቀድሞውን የአንድነትና ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሽበሺንና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ዛሬ በነፃ አሰናበተ፡፡
አዲስ አበባ —
የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ሦስተኛ ምድብ ችሎት የቀድሞውን የአንድነትና ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባል አቶ ዳንኤል ሽበሺንና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ዛሬ በነፃ አሰናበተ፡፡
ፍርድ ቤቱ በተሻረ የሕግ ድንጋጌ ሊከሰሱም ሆነ ሊቀጡ አይገባም ብሏል፡፡
ፍርድ ቤቱ ዛሬ ለብይን በቀጠረው መሰረት መዝገቡ በአለፈው ክረምት መመርመሩን በመግለፅ ሁለቱም ተከሳሾች ማለትም አቶ ዳንኤል ሽበሺ እና አቶ ኤልያስ ገብሩ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁ የተሻረ በመሆኑ ተከሳሾቹም በተሻረ የሕግ ድንጋጌ ሊከሰሱም ሆነ ሊቀጡ ስለማይገባ በነፃ ተሰናብተዋል ሲል መዝገቡንም መዝጋቱንም አስታወቀ፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
አቶ ዳንኤል ሽበሺንና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩን ፍርድ ቤት በነፃ አሰናበታቸው