የኢትዮጵያ መንግሥት በመድረኩና ኦፌኮ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና እንዲሁም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና በኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ ጃዋር መሐመድ ሲራጅ ላይ በትናንትናው ዕለት ክስ መስርቷል።
ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ መንግሥት በመድረኩና ኦፌኮ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና እንዲሁም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና በኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ ጃዋር መሐመድ ሲራጅ ላይ በትናንትናው ዕለት ክስ መስርቷል።
የክሱ ጭብጥ ምንድን ነው?
የግንቦት ሰባት መሪዎች፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ጠበቃ በክሱ ላይ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡
ግንቦት ሰባት ክሱን
“ቧልት” ሲለው፤
“ሕግና ሕገመንግሥት የሌለበት ሃገር፡፡” በማለት አስተዳድሩ በህወሃት የሕግና የሕገመንግሥት የበላይነት የሚንቀሳቀስ ሲል ክሱን አጣጥሏል።
በትናንትናው ዕለት ሦስቱ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የመገናኛ ብዙኃን መሪ የተመሰረተባቸው ክሶች የወንጀል ክሶች ናቸው። የመገናኛ ብዙሃኑ ኢሳትና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ የፀረ-ሽብር ሕጉ ተጠቅሶ ነው ክስ የተመሰረተባቸው፡፡
Your browser doesn’t support HTML5