የትግራይ ክልል ምክር ቤት የስድሥት ካብኔ አባላት ሹመት አፀደቀ

  • ግርማይ ገብሩ

መቀሌ

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት የስድስት ካብኔ አባላት ሹመት ዛሬ ማፅደቁ ተገለፀ፡፡

የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በአቶ አባይ ውልዱ ዛሬ ጠዋት የቀረበለትን ሹመት አፅድቋል፡፡

ምክር ቤቱ የስድስት ቢሮ ኃላፊዎች የክልሉ ከፍተኛ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሁም የክልሉ ዋና ኦዲተር ኮሚሽነርን ሹመት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የትግራይ ክልል ምክር ቤት የስድሥት ካብኔ አባላት ሹመት አፀደቀ