የኮረናቫይረስ በኢትዮጵያ ምን ያህል ጊዜ አለን?

Dr. Sosina Kebede and Dr. Dawd S. Siraj

ብርቱ የሚባሉትን ባለ ጸጋ አገሮች ጭምር እንዲህ ክፉኛ ያራደ ወረርሽኝ የጥድፊያ መዛመት ለመግታት በእርግጥ ምን ይሆን ማድረግ የሚቻለው?

እስካሁን በተለያዩ አገሮች የታዩት ሙከራዎች ባረጋገጡት ዕውነታ ለቫይረስሱ የተጋለጡ ሰዎች መኖራቸው በምርመራ በተረጋገጠ መጀመሪያዎቹ ቀናት፣ በወረርሽኙ የመጀመሪያ ደረጃ ወቅት መደረግ ሲገባቸው ያልተደረጉ አለያም ወሳኟ ሰዓት ያለፈባቸው እርምጃዎች የአደጋውን ጥናት ከሚወስኑ ጉዳዮች ቀዳሚዎቹ መሆናቸው ነው።

የቀናት ዕድሜ አመጡት የተባለው ፈተና ያስደምማል። ለኢትዮጵያም መሆን ያለበት በጊዜው ካልተፈጸመ እንዳይረፍድ ሥጋት መኖሩ ነው የተጠቆመው። ወረርሽኙን ለመዋጋት መጭው ቀናት ለኢትዮጵያ ወሳኝ መሆናቸውን በመጠቆም መንገድ ጠቋሚ ምክረ-ሃሳብ ያቀረቡ ባለሞያዎች ናቸው።ፕሮፌሰር ዳውድ ሰይድ ሲራጅ በዩናይትድ ስቴትሱ የዊስኮንሰን ዩኒቨርሲቲ የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና ትምሕርት መምሕር እና ከዓለም አቀፍ ጉዞ ጋር የተዛመዱ የሕክምና ጉዳዮች ክትትል ዲሬክተር ናቸው።ዶ/ር ሶስና ከበደ የውስጥ ደዌ ሕክምና እና የሕብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ባለሞያም ናቸው።

Your browser doesn’t support HTML5

የኮረናቫይረስ በኢትዮጵያ ምን ያህል ጊዜ አለን?.. ክፍል አንድ

Your browser doesn’t support HTML5

የውይይቱን ሁለተኛ ክፍል ከዚህ ያድምጡ

Your browser doesn’t support HTML5

ኮረናቫይረስ በኢትዮጵያ ምን ያህል ጊዜ አለን? - ክፍል ሶስት