በቻይና ሁበይ በኮሮናቫይረስ የሞቱት ሰዎች 254 ደረሰ

  • ቪኦኤ ዜና

ሁበይ በተባለው የቻይና ምዕከላዊ ክፍለ-ሃገር ተጨማሪ 254 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መሞታቸውን ባለሥልጣኖች ገልፀዋል። የበሽተኞች ብዛትም በከፍተኛ ደረጃ እንደጨመረ አስታውቀዋል።

በሁለት ወራት ውስጥ የተስፍፋው ኮሮናቫይረስ ማዕከል የሆነው ሁበይ ክፍለ-ሀገር የጤና ባለሥልጣኖች የምርመራ አሰራራቸውን በላብራቶሪ መሆኑ ቀርቶ መላ አካልን በኮፑተር ወደ ማየት መቀየራቸውን ተናግረዋል።

የበሽተኞች ብዛት በተከታታይ ለሁለት ቀናት ቀንሷል ስትል ቻይና ባስታወቀች ማግሥት ነው የአሁኑ የመባባስ ዜና የተሰማው።