ኮሮናቫይርስ በቻይና

  • ቪኦኤ ዜና

የቻይና ብሄራዊ የጤና ኮሚሽን ተጫማሪ 121 የኮሮናቫይርስ በሽተኞች መሞታቸውን ዛሬ ገልጿል። በበሽታው የሞቱት ሰዎች ብዛት 1,400 መድረሱን ጠቁሟል።

5,090 አዲስ በሽተኞች እንዳሉም ተናግሯል። የኮሚሽኑ ምክትል ኃላፊ ዜንግ ቲክሲን ለጋዜጠኞች ሲናገሩ 1,716 የጤና ሰራተኞች በቫይረሱ ታመዋል። ከእነሱም ስድስቱ ሞተዋል ብለዋል።

ከትላንት ማታ አንስቶ የታመሙት ሰዎች ብዛት 63,851 መድረሱ ታውቋል።